Skip to main content

Alcohol's Effects on Health

Research-based information on drinking and its impact.

የአልኮል መጠጥ እና አንጎል፦ አጠቃላይ እይታ (Amharic)

Image
image of the brain
Diffusion tensor imaging (DTI) የ58 አመት እድሜ ያለው የአልኮል አጠቃቀም ችግር ያለበት ሰውን ጭንቅላት የፋይበር ትራክ የሚያሳይ ነው። DTI በህይወት ባለ አንጎል ውስጥ የዋይት ማተር መሄጃ ካርታ ነው።
ምስል የ Adolf Pfefferbaum፣ የ Edith V. Sullivan, Ph.D. መልካም ፈቃድ ነው።

አልኮል በተግባቦት መተላለፊያ መንገድ ላይ እንቅፋት በመሆን የአእምሮን ገጽታ እና አሰራር ሊያደናቅፍ ይችላል። አልኮልን ከልክ በላይ መጠቀም ባላንስን፣ ማስታወስን፣ ንግግርንና ትክክለኛ ውሳኔ መስጠትን የሚቆጣጠሩ የአእምሮ አካባቢ ቦታዎች ሥራቸውን በትክክል እንዳይሰሩ በማድረግ፣ ጉዳትን እና ሌሎች አሉታዊ ነገሮችን ሊያስከትሉ ይችላሉ። የረዥም ጊዜ ከባድ የሆነ የመጠጣት ልምድ በነርቭ ሴሎች ላይ ለውጥን ያመጣል፣ ለምሳሌ መጠናቸው ይቀንሳል። ከዚህ በታች ከአልኮል እና ከአንጎል ጋር የተያያዙ ጥቂት ቁልፍ ርዕሶች አሉ።

የወጣትነት አንጎል 

የወጣትነት አንጎል ከአዋቂዎች አንጎል ይልቅ ለአልኮል አሉታዊ ተፅእኖዎች የበለጠ ተጋላጭ ናቸው። በወጣትነት ወቅት ላይ አልኮልን ያለአግባብ መጠቀም የአእምሮ እድገት አካሄድ ላይ ለውጥ ሊያስከትልና የዘላቂው የአእምሮ ውቅር ላይ ዘላቂ ለውጥ ሊያስከትል ይችላል። 

በአልኮል የሚመጡ ጊዜያዊ ራስን መሳቶች

አልኮሆል አላግባብ መጠቀም  በአልኮል ምክንያት የሚመጣ ጥቁር መጥፋት ያስከትል ይችላል። ጊዜያዊ ራስን መሳቶች በግለሰቡ የማስታወስ ችሎታ ውስጥ ያሉ ክፍተቶች ሲሆኑ በሚሰክሩበት ጊዜ የሚፈጠሩ ክስተቶች ናቸው። እነዚህ ክፍተቶች የሚከሰቱት ትዉስታዎችን ከአጭር ጊዜ ወደ ረጅም ጊዜ ክምችት ማለትም በአንጎል ክፍል - ማህደረ ትውስታ ማጠናከሪያ በመባል የሚታወቀው - ሂፖካምፐስ (hippocampus) የሚባሉ የማስታወስ ማጠናከሪያዎች መተላለፍ በጊዜያዊነት ለመገደብ በሚል ግለሰቡ በቂ አልኮል ሲወስድ ነዉ።

ከመጠን በላይ የሆነ አልኮል መውሰድ

ጉልህ የሚባሉ እክሎች መኖራቸውን የሚጠቁሙ ግልጽ ምልክቶች ቢኖሩም መጠጣትን መቀጠል ከልክ በላይ አልኮል መጠጣትን ሊያስከትል ይችላል። አልኮል ከመጠን በላይ የመጠጣት ችግር የሚከሰተው በደም ዝውውር ውስጥ የአልኮል መጠጥ በብዛት ከመኖሩ የተነሳ እንደ መተንፈስ፣ የልብ ምትና የሰውነት ሙቀት መቆጣጠር ያሉ መሠረታዊ የሕይወትን ድጋፍ ተግባራትን የሚቆጣጠሩት የአእምሯችን ክፍሎች ስራቸውን ማቆም በሚጀምሩበት ጊዜ ነው። ከመጠን በላይ የመጠጣት ምልክቶች የአእምሮ ግራ መጋባት፣ የንቃተ ህሊና ችግር፣ ማስመለስ፣ ለመተንፈስ መቸገር፣ የልብ ምት ፍጥነት መቀነስ፣ ያላበው ቆዳ፣ ቋቅ አለማለት (መታነቅን የሚከላከል) እና እጅግ ዝቅተኛ የሰውነት ሙቀት የመሳሰሉ የደነዘዙ ምላሾች ናቸው። ከመጠን በላይ አልኮል መጠጣት በአንጎል ላይ ዘላቂ ጉዳት ወይም ሞት ሊያስከትል ይችላል።

የአልኮል ጠጭነት ህመም

ግለሰቦች አልኮል እየጠጡ በሄዱ ቁጥር፣ ከጊዜ በኋላ ቀጣይ የሆኑ ለውጦች የአእምሮ ውቅርና አሰራር ላይ ሊፈጠር ይችላሉ። እነዝህ ለውጦች የአእምሮን ሥራ በማደናቀፍ በቁጥጥር ሥር የነበረ አልኮልን በተወሰነ ጊዜ መጠቀምን  ወደ መደበኛ ያለአግባብ መጠቀም በማምራት መቆጣጠር ወደማይቻለው የአልኮል አጠቃቀም በሽታ (AUD) ያመራል። ከመለስተኛ እስከ ከፍተኛ AUD ያለባቸው ሰዎች የአልኮል ሱሰኝነት አዙሪት ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ። የረጅም ጊዜ ሳይጠጡ መቆየትን ተከትሎ፣ አእምሮ ወደ መደበኛ ሁኔታው የመመለስ ችሎታ መጠን ሙሉ በሙሉ የሚታወቅ አይደለም፣ ነገር ግን ቁጥራቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ቢያንስ አንዳንድ በAUD-የተፈጠሩ የአንጎል ለውጦች—እና የአስተሳሰብ፣ የስሜቶች እና የባህሪ ለውጦች እና አብረዋቸው የሚሄዱ ባህሪያት—ሊሻሻሉ እና ምናልባትም ለወራት ከመጠጣት መታቀብ ጋር ሊሆኑ ይችላሉ። (ስለ AUD ነርቭ ሳይንስ የበለጠ ዝርዝር መረጃ በ Neuroscience: The Brain in Addiction and Recovery ክፍል The Healthcare Professional’s Core Resource on Alcoholላይ ቀርቧል።)

በቅድመ-ወሊድ ያለ የአልኮል መጋለጥ

በቅድመ-ወሊድ ያለ የአልኮል መጋለጥ በልጅነት ጊዜ በማንኛውም ጊዜ ሊታዩ የሚችሉ የተለያዩ የእድገት፣ የእውቀት እና የባህሪ ችግሮች በማስከተል አንጎልን ሊጎዳ ይችላል። በመጀመሪያዎቹ ደረጃዎች እና አንዲት ሴት ነፍሰ ጡር መሆኗን ከማወቁ በፊት ጨምሮ አልኮል በእርግዝና ወቅት በማንኛውም ደረጃ የፅንስ እድገትን ሊያስተጓጉል ይችላል።

ስለ አልኮሆል እና የአንጎል ጤና የበለጠ መረጃ ለማግኘት፣ እባክዎ የ Alcohol and the Brain የሚለውን ገጽ ይጎብኙ።

Looking for U.S. government information and services?
Visit USA.gov